Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 784 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ 7 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 139 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 784 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 75 ሺህ 368 ደርሷል።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የ7 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በዚህም በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎቸ ቁጥር 1 ሺህ 198 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ ያሰፈሩት መረጃ ያመለክታል።

በ24 ሰዓታት ውስጥ 199 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 31 ሺህ 204 ደርሷል።
እንዲሁም 269 ፅኑ ህሙማን የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.