Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 916 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ17 ሰዎች ሕይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 15 ሺህ 561 የላብራቶሪ ምርመራ 916 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 61 ሺህ 700 መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

በ24 ሰዓታት ውስጥ የ17 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 966 ደርሷል።

በትናንትናው ዕለት 377 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 23 ሺህ 54 መድረሱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

እንዲሁም 319 ፅኑ ህሙማን የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

እስከአሁን በኢትዮጵያ 1 ሚሊየን 93 ሺህ 830 የላብራቶሪ እንደተረገ መረጃው አመልክቷል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.