Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 3 ወራት 55 ቢሊየን ብር ብድር ተሰጥቷል- ብሄራዊ ባንክ

በሶስት ወራት ከተሰጠው ብድር 85 በመቶ የሚሆነው ለግሉ ዘርፍ የተሰጠ መሆኑን የብሄራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ ተናግረዋል፡፡
ዶክተር ይናገር ከሀምሌ እስከ መስከረም የነበረውን የእቅድ አፈፃፀም በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸው በሶስቱ ወራት በባንኮች ያለው የቁጠባ መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ የቁጠባ መጠን በስድስት እጥፍ ብልጫ እንዳለው አንስተዋል።
ባንኮች ያለባቸውን የጥሬ ገንዘብ እጥረት ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ ስራዎች ተከናውነው ውጤት ማስመዝገባቸውንም ዶክተር ይናገር ጠቁመዋል።
ባለፉት ሶስት ወራት የዋጋ ንረትን ከመቆጣጠር፣ የውጭ ምንዛሬ ከማሳደግ፣ የፋይናንስ ዘርፉን ጤናማ ከማድረግ፣ ከፋይናንስ ተደራሽነት እና አካታችነትን
ከማሻሻል እንዲሁም የቁጠባ እና ኢንቨስትመንት ስራዎች አንጻር ባንኩ ያከናወናቸው ስራዎችም በመግለጫው ተነስተዋል፡፡
እንዲሁም ተቋሙ እያካሄደ ከሚገኘው የሪፎርም ስራ ጋር ተያይዞ በተከናወኑ ስራዎች ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
በለይኩን ዓለም
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.