Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 7 ወራት ለዓለም ገበያ ከቀረበ ቡና 407 ሚሊየን ዶላር ተገኘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት ሰባት ወራት ለዓለም አቀፍ ገበያ ከቀረበ ቡና 407 ሚሊየን ዶላር መገኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን አስታወቀ።

በሰባት ወራቱ 150 ሺህ ቶን ቡና ለዓለም አቀፉ ገበያ የተላከ ቢሆንም፥ የተገኘው ገቢ ከዛሬ 10 ዓመት በፊት ከነበረው ያነሰ መሆኑን የባለስልጣኑ ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ደበላ ገልፀዋል።

በመጠን ከፍተኛ ቡና ለውጪ ገበያ ቢቀርብም የቡና ገበያ በመቀዛቀዙ ምክንያት የተገኘው ገቢ ዝቅተኛ መሆኑን አንስተዋል።

ይህንን በማስተካከል ገቢውን ለማሳደግ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

አያይዘውም ኢትዮጵያ የፊታችን ሐሙስ የቡና ጥራት ላይ ያተኮረ ምክክር ለመጀመሪያ ጊዜ ታስተናግዳለች ብለዋል።

በቢንያም ሲሳይ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.