Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 9 ወራት ከ248 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 248 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
 
ሚኒስቴሩ በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 267 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 93 በመቶውን ማሳካት መቻሉ ተመላክቷል፡፡
 
የተሰበሰበው ግብር ከአገር ውስጥ ታክስ ከ145 ነጥብ 2 ቢሊየን በላይ  ሲሆን÷ከ103 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ የሚሆነው ደግሞ ከወጪ ንግድ ቀረጥና ታክስ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
 
ከ2013 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ17 ከመቶ እድገት እንዳለው ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው ÷ አፈጻጸሙ የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመው ÷ለዚህ ውጤት መመዝገብ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅበዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.