Fana: At a Speed of Life!

ባንኩ በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን የዲጂታል ማዕከል ከፈተ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን የዲጂታል ማዕከል በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።

አዲሱ የዲጂታል ማዕከል ከ 20 በላይ የገንዘብ መክፈያና መቀበያ ማሽኖችን በአንድ ቦታ በማስቀመጥ ደንበኞች በቀላሉ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላል ተብሏል።

ማዕከሉ ከፍተኛ የደንበኞች ፍሰት ባለበት መገናኛ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ህዳሴ ህንፃ ላይ ነው የተከፈተው።

በዲጂታል ማዕከሉ ውስጥ ከተቀመጡ በርካታ የገንዘብ መክፈያና መቀበያ ማሽኖች መካከል ሁለቱ ገንዘብ ገቢና ወጪ ማድረግ እንዲችሉ ተደርገው የተዘጋጁ መሆናቸው ተገልጿል።

በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የባንኩ ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ባጫ ጊና፥ በቀጣይ ተመሳሳይ ገንዘብ ገቢና ወጪ የሚያደርጉ ከ100 በላይ ተጨማሪ የገንዘብ መክፈያና መቀበያ ማሽኖች በተለያዩ አካባቢዎች የሚቀመጡ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአሁኑ ወቅት ከ1ሺህ 560 በላይ በሚሆኑ ቅርንጫፎች ከ23 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ደንበኞችን ማፍራት መቻሉን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከ3ሺህ በላይ የገንዘብ መክፈያ ማሽኖች ያሉት ባንኩ፥ ከአምስት ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ የኤቲኤም ካርድ ተጠቃሚ ደንበኞችም አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.