Fana: At a Speed of Life!

ባንግላዴሽ የተ.መ.ድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በኢትዮጵያ ላይ ያሰማውን ድምጽ እንድትቃወም ተጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ትዝታ ሙሉጌታ በህንድ ከባንግላዴሽ ምክትል ከፍተኛ ኮሚሽር ኑራል ኢስላም ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም አምባሳደር ትዝታ፥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርገውን ስብሰባ እና ውጤቱን የባንግላዴሽ መንግስት እንዲቃወም ጠይቀዋል፡፡

አምባሳደሯ የኢትዮጵያ መንግስት በሰሜን ኢትዮጵያ ተፈፅሟል ስለተባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በጋራ በተሰጠው ምክረ ሀሳብ መሠረት ተግባራዊ ለማድረግ ተስማምቶ ወደተግባር ቢገባም፥ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ይህን ሃቅ ወደ ጎን በመተው በኢትዮጵያ ላይ ያነሳው ሃሳብ ኮሚሽኑ ላይ ሀገሪቱ ያላትን እምነት የሚሸረሽር ሆኖ እንዳገኘችው አስረድተዋል።

የባንግላዴሽ መንግስት የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት አባል እንደመሆኑ ጉዳዩን በትኩረት እንዲከታተለውና በኮሚሽኑ የተሰጠውን ሃሳብ በፖለቲካ የተቃኘ መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት መቀልበስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንዲሰራም ጠይቀዋል።

አምባሳደሯ በውይይታቸው ወቅት የኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ የሚያደርገውን ያላሰለሰ ጥረት፣ በአማራና በአፋር ክልሎች በአሸባሪው ህወሓት የደረሰውን እና እየደረሰ ያለውን አስከፊ ግፍ እና ቡድኑ በመሠረተ – ልማት ላይ ያደረሰውን ውድመት በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በህንድ የባንግላዴሽ ምክትል ከፍተኛ ኮሚሽነር ኑራል ኢስላም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለተሰጣቸው ገለጻ አመስግነው የኢትዮጵያ መንግስት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማጣራትና የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ ያደረገውን ጥረት ማድነቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.