Fana: At a Speed of Life!

ባይደንና ሃሪስ የታይም መጽሔት የዓመቱ ሰዎች በመባል ተመረጡ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በቅርቡ ስልጣን የሚይዙት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንና ምክትላቸው ካሚላ ሃሪስ የታይም መጽሔት የዓመቱ ሰዎች በመባል ተመረጡ፡፡

ታይም በትዊተር መልዕክቱ የባይደንና ሃሪስ ጉዞ ታሪካዊ ነበር ሲል አስፍሯል፡፡

ባይደንና ሃሪስ ለዚህ የበቁት ኮቪድ በመከላከል ከፊት የቆሙ የጤና ባለሙያዎችንና የአሜሪካ የተላላፊ በሽታዎች ተቋም ኃላፊ አንቶኒዮ ፉቺ እና ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን በመርታት ነው ተብሏል፡፡

የታይም መጽሔት ዋና አዘጋጅ ኤድዋርድ የአሜሪካንን ታሪክ በመቀየራቸው ከመከፋፈል ይልቅ የአብሮነት ኃይል እንደሚልቅ በማሳየታቸው ባይደንና ሃሪስ የ2020 የዓመቱ ሰው በመሆን መመረጣቸውን ነው በትዊተሩ ያሰፈረው፡፡

በ2016 ትራምፕ ወደ ስልጣን ሲመጡ በተመሳሳይ የዓመቱ ሰው መባላቸው ይታወቃል፡፡

ታይም በየዓመቱ በአሉታም ይሁን በአወንታ ተጽዕኖ ያሳረፉ ሰዎችን መምረጥ የጀመረው ከአውሮፓውያኑ 1927 ጀምሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.