Fana: At a Speed of Life!

ቤላሩስ የሩሲያ ወሳኝ ስትራቴጂያዊ አጋር ናት – የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቤላሩስ የሩሲያ ወሳኝ ስትራቴጂያዊ አጋር አገር ናት ሲሉ የሩሲያው መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ ተናገሩ፡፡

ቤላሩስ እና ሩሲያ  በጋራ የወታደራዊ  እቅዶች እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ ውይይት መድረክ አካሂደዋል፡፡

በውይይታቸውም የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ÷የምዕራቡ ዓለም እያወጀ ያለውን ቀጥተኛ ያልሆነ ጦርነት ለመመከት ሞስኮ እና ሚንስክ ወታደራዊ አቅማቸውን ለማጠናከር ወሳኝ እርምጃዎችን መውስድ አለባቸው ብለዋል፡፡

ቤላሩስ የእኛ አስፈላጊ ስትራቴጂያዊ አጋራችን ናት ያሉት ሚኒስትሩ÷ በአሁኑ ሰዓት የምዕራባውያንን ያልታወጀ ጦርነት ለመመከት በሁለቱ አገራት ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት እየተጠናከረ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ሁኔታዎቸ ሁለቱ አገራት የመከላከያ አቅማቸውን ለማጠናከር አስፈላጊ እርምጃዎችን መውሰድ እንዳለባቸው ያመላክታሉ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፡፡

ስለሆነም ሩሲያ  የአየር መከላከያ ስርዓትን ጨምሮ ቤላሩስ የሚስፈልጋትን ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ  ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡

ቤላሩስ የአሜሪካንና አጋሮቿን ፀብ አጫሪነት ለመቋቋም ያሳየችውን ቁርጠኝነት ያደነቁት ሰርጌይ ሾይጉ÷ የሚነስክ ልዑካን ቡድን አባላት ሞስኮ በቀጣይ በምታዘጋጀው የፀጥታ ኮንፈረንስ እንዲሳተፉ ጋብዘዋል፡፡

ቤላሩስ አሁን ባለው የዩክሬን ጦርነት ው ተሳትፎ የሌላት ቢሆንም አሜሪካ እና አጋሮቿ ግን ከሩሲያ ተዛማጅ ማዕቀቦችን ጥለውባታል።

ሩሲያ እና ቤላሩስ በፈረንጆቹ 1999 የጋራ ካቢኔ ፣ ፓርላማ ፣ ፍርድ ቤቶች እና ሌሎች ተቋማት ለመመስረት በማቀድ የሁለትዮሽ ህብረት ስምምነት መፈራረማቸውን አር ቲ በዘገባው አስታውሷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.