Fana: At a Speed of Life!

ቤንያሚን ኔታንያሁ በቀረበባቸው የሙስና ክስ ላይ የመጀመሪያ ምስክር መሰማት ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2013 (ኤፍ .ቢ.ሲ) የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በቀረበባቸው የሙስና ክስ ላይ የመጀመሪያ ምስክር መሰማት ጀምሯል።
ኔታንያሁም በምስክር ማሰማት ሂደቱ ላይ ችሎት መገኘታቸው ተነግሯል፡፡
የ71 ዓመቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በሶስት የተለያዩ ጉዳዮች በጉቦ፣ በማጭበርበር እና እምነት በማጉደል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡
ይሁን እንጅ ኔታንያሁ ባለፈው ወር በተሰየመው ችሎት ጥፋተኛ አይደለሁም ሲሉ ተደምጠዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፍርድ ሂደት ከኮሮቫይረስ ጋር በተያያዙ ገደቦች እና ባለፈው ወር በተካሄደው ምርጫ ምክንያት ለበርካታ ጊዜ መዘግቱ ይነገራል።
ምርጫው ላለፉት ሁለት ዓመታት በእስራኤል ፖለቲካ ውስጥ ያለውን ችግር ማስቆም አልተቻለም ነው የተባለው።
ፕሬዝዳንት ሬቨን ሪቭሊን በዛሬው እለት የፓርቲ መሪዎችን የሚያማክሩ ሲሆን አዲስ ጥምር መንግስት ለመመስረት የተሻለ እድል አለው ያሉትን ፓርቲ ይሰይማሉም ነው የተባለው ፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ተፎካካሪዎች ኔታንያሁ ስልጣን ላይ ከቆዩ ያለመከሰስ መብት የሚሰጣቸውን ህግ ሊከተሉ ይችላሉ በሚል ፍራቻቸውን እየገለጹ ነው፡፡
ምንጭ፦ ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.