Fana: At a Speed of Life!

ብልጽግና ፓርቲ “ነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ሃገራዊ ዘመቻን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፓርቲው “ነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ-መንግስት” ሃገራዊ ዘመቻን መቀላቀሉን በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የፋይናንስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘነበ ኩማ ገለጹ፡፡
በአሁኑ ሰዓት በሃገራችን ላይ ያለአግባብ በአሜሪካ መንግስት በኩል እየተደረገ ያለውን ጫና በመቃወም እውነታውን ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ማሳወቅ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት መሆን ይገባዋልም ነው ያሉት አቶ ዘነበ፡፡
የብልጽግና ፓርቲ አመራሮችና ሰራተኞች በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ሰላም በማስከበር ግዳጅ ላይ መስዋትነት እየከፈለ ለሚገኘው የሃገር መከላከያ ሠራዊት የደም ልገሳ እና የአንድ ወር ደመወዛቸውን ድጋፍ በመለገስ አጋርነታቸውን ማሳየታቸው ይታወሳል፡፡
በሃገር አቀፍ ደረጃ የተያዘው ዘመቻም እንዲሳካ የራሱን አስተዋጾኦ ለማድረግ ጽህፈት ቤቱ “ነጩ ፖስታ ወደ ነጩ ቤተ- መንግስት” ዘመቻን የተቀላቀለ ሲሆን÷ አሜሪካ ከእውነታው በማፈንገጥ በአሸባሪው ቡድን የተጋረጠብንን አደጋ ለመመከት የሚደረገውን ትግል ለማደናቀፍ በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ ለመግባት የምታደረገው ሙከራ እንድታቆም ተጠይቋል።
በዘመቻው በጽህፈት ቤቱ የሚገኙ አመራሮች አና ሰራተኞች መሳተፋቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በተመሳሳይ የሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች ዘመቻውን ተቀላቅለዋል፡፡
በዚሁ ወቅት የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አየለች እሸቴ እንደገለጹት÷ የ”ነጩ ፖስታ ለነጩ ቤተመንግስት” የንቅናቄ ዘመቻ ሀገራችን በዓለም አደባባይ ያላትን ገጽታ ለማበላሻት በተጠና መልኩ እየተንቀሳሰቀሱ ያሉ ሃይሎችን መረጃ ሃሰት መሆኑን ለማሳወቅ እና መሬት ላይ በተጨባጭ ያለውን ዕውነታ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳየት ያለመ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.