Fana: At a Speed of Life!

ብልጽግና ፓርቲ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ በመላው ዓለም ለሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባዘጋጀው ውይይት ላይ ተሳተፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብልጽግና ፓርቲ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ በመላው ዓለም ለሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባዘጋጀው የበይነመረብ ውይይት ላይ ተሳተፈ፡፡

ብልጽግና ፓርቲን በመወከል የፓርቲው የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

ዶክተር ቢቂላ ቻይና በጤናና በድህነት ቅነሳ ስራ ላይ ያስመዘገበችው ስኬት ለአፍሪካና ለሌሎች የዓለም አገራት ምሳሌ ነው ሲሉ በውይይቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡

በቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ አዘጋጅነት የተካሄደው ይህ ውይይት የብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ ከ80 ሀገራት የተወጣጡ ከ300 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፈውበታል፡፡

ውይይቱ “የተሻለች ዓለም ለሁሉም” በሚል መሪ ቃል የድህነት ቅነሳን ትኩረት በማድረግ የተካሄደ ሲሆን የቻይና የድህነት ቅነሳ ዘመቻና ፕሮግራም ቻይና እንዴት በአጭር ጊዜ በተቀናጀ አካሄድ ከድህነት እንደወጣች ለዓለም አገራት ተሞክሮ መቅረቡ ነው የተገለጸው፡፡

በፈረንጆቹ 2020 መጀመሪያ ላይ ሙሉ በሙሉ ከድህነት የወጣችው የቻይናዋ የዣንዥግ ግዛት በውይይቱ ወቅት እንደምሳሌ ተነስታለች፡፡

ቻይና በቅርቡ በመላው ግዛቷ 750 ሚሊዮን ዜጎቿን ከድህነት ሙሉ በሙሉ ማውጣቷ ይታወሳል፡፡

በውይይቱ ከድህነት ቅነሳ በተጨማሪ የጤና ጥበቃ ስርዓት እንዲሁም ሽብርተኝነትን በመከላከል የዜጎችን ሰላም ከመጠበቅ አንጻር የቻይና ተሞክሮ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

ከአፍሪካ የሶስት አገራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም ብልጽግና፣ የግብጽና የቶጎ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሀሳባቸውንና አስተያየታቸውን አቅርበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.