Fana: At a Speed of Life!

ብሪታኒያ ማሽተትና ጣዕም ማጣትን የኮሮናቫይረስ ምልክቶች ዝርዝር ውስጥ አካተተች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በብሪታኒያ ሰዎች ራሳቸውን ችለው እንዲገለሉ ከሚያደርጉ  የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ዝርዝር ውስጥ ማሽተት አለመቻል ወይም ጣዕም ማጣትን ማካተቷ ተነግሯል ።

እስካሁን ድረስ ሰዎች ራሳቸውን የሚያገሉት ትኩሳትና ማሳል  ምልክት ብቻ ሲኖርባቸው ሲሆን፥ ይህ ደግሞ ሰዎች በበሽታው ተይዘው ኢንፌክሽኑን  ሊያስተላልፉ ይችላሉ በሚል ነው የተባለው።

በዚህም መሰረት ሰዎች  አዲስ፣ ቀጣይነት ያለው ሳል፣ ትኩሳት፣ ማሽተት ወይም ጣዕምን ማጣት ምልክቶች መካከል አንዱን ካሳዩ ሌሎች ላይ የኮሮና ቫይረስ የማስተላለፍ እድልን ለመቀነስ ለሰባት ቀናት ራሳቸውን  አግልለው እንዲቆዩም መክረዋል።

የጆሮ፣ የአፍንጫ  እና የጉሮሮ ሐኪሞች  ተጨማሪ ምልክቶች የኮሮና ቫይረስ ምልክት  ዝርዝር ውስጥ መካተት አለባቸው በማለት  ለሳምንታት ማስጠንቀቂያ ሲሰጡ ነበር።

ከዚያም ባለፈ የሳይንስ አማካሪዎች መንግሥት የኮሮና ቫይረስ ምልክት ተደርገው የተቀመጡትን ምልክቶች እንዲከልስ ሀሳብ መስጠታቸውም ነው የተነገረው።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.