Fana: At a Speed of Life!

ብሪታኒያ የሁዋዌ 5ኛ ትውልድ ኔትወርክ በተወሰነ ገደብ ስራውን እንዲቀጥል ውሳኔ አሳለፈች

አዲስ አበባ፣ጥር 19፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ብሪታኒያ የቻይናው ሁዋዌ 5ኛ ትውልድ (5G) ኔትወርክ በተወሰነ ገደብ በሀገሯ ስራውን እንዲቀጥል ውሳኔ አሳለፈች፡፡

ውሳኔው የተላለፈው ብሪታኒያ ኩባንያውን እንድታግደው አሜሪካ ጫና እየፈጠረች ባለችበት ወቅት፡፡

ብሪታኒያ ውሣኔውን ያሳለፈችው በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ገደብ በመጣል ነው ተብሏል፡፡

በዚህም  ኩባንያው  ከፍተኛ ጥንቃቄ  የሚፈልገው ወሳኝ ክፍል (ኮር) ተብሎ የሚጠራውን  አካል እንዳያቀርብ  እገዳ ተጥሎበታል፡፡

ሁዋዌ ኩባንያ በብሪታኒያ 35 በመቶ በሚሆነው 5ኛ ትውልድ ኔትወርክ ዝርጋት እንዲሰማራ  እንደተፈቀደለት ተነግሯል፡፡

በተጨማሪም ከወታደራዊ ማዕከላት እና ከኒውክሌር ጣቢያዎች አቅራቢያ እቀባ እንደተጣለበት ነው የተገለጸው፡፡

ቤጂንግ ኩባንያው  ከታገደ በብሪታኒያ ሌሎች የንግድ እና የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ከፍተኛ እርምጃ  እንደምትወስድ አስጠንቅቃ ነበር፡

ኩባንያው በበኩሉ ይህ መፈቀዱ ብሪታኒያ የዓለም-መሪ ቴክኖሎጂን ማግኘት እንድትችል እና ተወዳዳሪ የሆነ ገበያ እንዲኖራት ያደርጋል ብለዋል፡፡

አያይዘውም የ5G ልቀትን ለማስቀጠል ከደንበኞቻችን ጋር አብረን መሥራታችን እንደምንቀጥል ለብሪታኒያ መንግስት እናረጋግጣለን ማለታቸው ነው የተነገረው፡፡

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.