Fana: At a Speed of Life!

ብሪታንያ እና ካናዳ በቤላሩሱ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ላይ እገዳ ጣሉ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሪታንያ እና ካናዳ በቤላሩሱ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ላይ እገዳ ጣሉ፡፡

ሃገራቱ በፕሬዚዳንቱ ላይ በሃገሪቱ ከተካሄደው ምርጫ እና እሱን ተከትሎ በተቃዋሚዎች ላይ ተፈጽሟል ከተባለው የሃይል እርምጃ ጋር ተያይዞ የጉዞ እና ንብረታቸው ላይ እገዳ ጥለዋል፡፡

ከፕሬዚዳንቱ በተጨማሪም ልጃቸውን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት እገዳ ተጥሏል፡፡

እገዳው ፕሬዚዳንቱና ባለስልጣናቱ ላይ የጉዞ ክልከላን እና ንብረታቸው እንዳይንቀሳቀስ የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡

ባለፈው ነሃሴ ወር ላይ በተካሄደው ምርጫ ፕሬዚዳንት ሉካሼንኮ አሸናፊ እንደሆኑ መገለጹ ይታወሳል፡፡

ተቀናቃኞቻቸው ደግሞ የምርጫው ውጤት ተጭበርብሯል ብለዋል፤ ይህን ተከትሎም በርካታ ቤላሩሲያውያን ለተቃውሞ አደባባይ መውጣታቸው የሚታወስ ነው፡፡

መንግስትም ከዚህ ጋር ተያይዞ ከ12 ሺህ በላይ ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

ምዕራባውያን ደግሞ የሉካሼንኮ አስተዳደር ምርጫውን አጭበርብሯል፤ በተቃዋሚዎች ላይም የሃይል እርምጃ ወስዷል በሚል ይወነጅላሉ፡፡

የእርሳቸው አስተዳደር ህገ ወጥ ነው በሚልም እውቅናን ይነፍጉታል፡፡

ምንጭ፥ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.