Fana: At a Speed of Life!

ብሪታንያ የኮቪድ-19 ክትባትን መስጠት ጀመረች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሪታንያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ያግዛል ያለችውን ክትባት መስጠት ጀምራለች፡፡

ፋይዘር እና ባዮንቴክ የተሰኙና ኮቪድ-19ኝን ለመከላከል ያግዛሉ ያለቻቸውን ክትባት መስጠት መጀመሯ ተሰምቷል፡፡

በሃገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ባሳለፍነው ሳምንት ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ መስጠቷ የሚታወስ ሲሆን ይህም ከምዕራባውያን ሃገራት መካከል የመጀመሪያዋ ያደርጋታል ተብሏል፡፡

የሃገሪቱ መንግስት 20 ሚሊየን ሰዎችን መከተብ የሚችል 40 ሚሊየን መጠን ያለው ክትባት ማዘዙ የተሰማ ሲሆን 10 ሚሊየን ያህሉን በቀናት ውስጥ እንደሚረከብ ይጠበቃል፡፡

ክትባቱን በመጀመሪያ ዙር የጤና ባለሙያዎችና ዕድሜያቸው ከ80 ዓመት በላይ የሆናቸው የሚወስዱ ሲሆን፤ በሁለተኛው ዙር ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ የሆናቸው እና የጤና እክል ላለባቸው ወጣቶች ይሰጣል መባሉ የሚታወስ ነው፡፡

እስካሁን በዓለም ዙሪያ ከ67 ሚሊየን 900 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከ1 ሚሊየን 550 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ እና ዎርልድ ኦ ሜትር

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.