Fana: At a Speed of Life!

“ብርሃን የሚገኘው በአምፖል ነው”- ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ብርሃን የሚገኘው በአምፖል ነው” ሲሉ የጭዳ-ጅማ የመንገድ ግንባታን ባስጀመሩበት መረሃ-ግብር ላይ ገልጸዋል፡፡

ጅማ እና አካባቢው ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ስፍራዎች አንደኛው ቢሆንም ባለፉት 30 ዓመታት መንግሥት ትኩረት ሳይሰጠው በመቆየቱ ፈጣን ለውጥ ማምጣት ተስኖት ነበር ብለዋል፡፡

አሁን ግን ለጅማ እና አካባቢው ነዋሪዎቿ ፀሃይ ወጥቶላቸዋል ብለዋል፡፡

የጭዳ-ጅማ አስፋልት መንገድ ደግሞ በበርካታ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ሃብቶች ለታደለው የጅማና አካባቢው ህዝብ ወደ ብርሃን የሚወስድ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ሆኖም “ብርሃን ያለ አምፖል ምንም ስለሆነ አምፖሉን ጠበቅ በማድረግ የጋራ ብልፅግናውን ማየት ያስፈልጋል”ም ብለዋል፡፡

በጅማ አባ ጅፋር እና በኮንታ ታላላቅ ሰዎች መካከል የነበረው ወንድማማችነት ጠንካራ እንደነበረ ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የጭዳ-ጅማ መንገድም የኮንታ እና የጅማ አካባቢ ነዋሪዎችን የቀደመ ማህበራዊ ትስስር እንደገና የሚያጠናክር መሆኑን ገልፀዋል፡፡

መንግሥት በመንገድ ፕሮጀክቱ የገባውን ቃል በተግባር የሚያሳይ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡

 

በሶዶ ለማ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.