Fana: At a Speed of Life!

ብርቅዬ የዝሆን ዝርያዎችን ጠብቆ ለማቆየት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል – የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ የሚገኙ ብርቅዬ የዝሆን ዝርያዎችን ጠብቆ ለማቆየት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጠለያው የተጋረጠውን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል የውይይት መድረክ በጅግጅጋ ተካሂዷል።

የኃይለማርያም እና ሮማን ፋውንዴሽን መስራችና የቀድሞ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ፣ የኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አዲሱ አረጋ፣ የአካባቢ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ እና ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት በውይይቱ ተሳትፈዋል።

በመድረኩ በተለያየ ወቅት የአካባቢው ማህበረሰብ በመጠለያው ላይ የሚያደርገው የሰፈራ እና የግጦሽ እንቅስቃሴ መጠለያውን አደጋ ላይ ጥሎታል ተብሏል።

በተጨማሪም ህገወጥ የአደን እና ህገ ወጥ የዱር እንስሳት ንግድ ሌላው የዱር እንስሳቱን ቁጥር እያመናመነ ያለ ተግባር መሆኑን ኢቢሲ ዘግቧል።

ውይይቱ በመጠለያው የተጋረጠውን ችግር ለመቅረፍ በሶማሌና በኦሮሚያ ክልል የተሰሩ ስራዎችን በመገምገም በቀጣይ በህብረተሰቡ ውስጥ የባለቤትነት ስሜት በመፍጠር እና ተጠቃሚ በማድረግ የችግሩ ባለቤት የሆኑትን አካላት ለችግሩ መፍትሄ እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.