Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ ምርጫ በተጠናቀቀባቸው ቦታዎች የምርጫ ጣቢያ መዝጋት እና ቆጠራ መጀመር እንደሚቻል አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዜጎች መርጠው ባጠናቀቁባቸው እና ለመምረጥ የተሰለፉ ዜጎች በተጠናቀቁበት ቦታዎች የምርጫ ጣቢያ መዝጋት እና የቆጠራ ስራ መጀመር እንደሚቻል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

6ኛው ሃገራዊ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ስነ ስርአት እየተካሄደ መሆኑን አንስቷል፡፡

የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ዘግይቶ የተጀመረባቸው ቦታዎች እንዲሁም የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ላይ የቁሳቁስ ስርጭት የዘገየባቸው ቦታዎች መኖራቸውንም ጠቅሷል፡፡

ከዚህ ባለፈም ድምፅ ለመስጠት ረጅም ሰልፍ ላይ ያሉ ዜጎች በመኖራቸው የድምፅ አሰጣጥ ሂደት እስከ ምሽቱ 3 ሰአት ድረስ መራዘሙን ቦርዱ አስታውሷል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም የምርጫ አስፈፃሚዎች እስከ ምሽት 3 ሰአት ድረስ የሚመጣ ማንኛውንም መራጭ እንዲያስተናግዱም ጥሪ አቅርቧል።

ነገር ግን የመራጮች መዝገባቸው ላይ ያሉ ዜጎች መርጠው ባጠናቀቁባቸው እና ለመምረጥ የተሰለፉ ዜጎች በተጠናቀቁበት ቦታዎች የምርጫ ጣቢያ መዝጋት እና የቆጠራ ስራ መጀመር እንደሚቻል ገልጿል።

በድምፅ አሰጣት ሂደት ወቅት ችግር ያጋጠማቸው ዜጎች 778 ነጻ የስልክ መስመር በመደወል ማሳወቅ ይችላሉም ነው ያለው ቦርዱ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.