Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ በመራጮች ትምህርትና መረጃ አሰጣጥ ዙሪያ ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር ምክክር አካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ትምህርት እና መረጃ አሰጣጥን አስመልክቶ ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር ምክክር አካሂዷል።

ቦርዱ የመገናኛ ብዙሃን ተደራሽነት እና ሚና ለመራጮች ትምህርት በሚል ርዕስ ነው የምክክር መድረኩን በዛሬው እለት ያካሄደው።

የመራጮች ትምህርት አይነትና የጊዜ ሰሌዳ፣ የምርጫ አዘጋገብ፣ ስነ ምግባር እና አሰራርን ለመደንገግ የወጣ መመሪያ የውይይት መድረኩ ትኩረት ናቸው።

የሚዲያ ሚና፣ ተደራሽነት እና ነባራዊ ሁኔታ፣ የኢትዮጵያ ህጎችና ዓለም አቀፍ ተሞክሮ፣ ከምርጫ አዘጋገብ አንፃር ሌላው የውይይት ነጥብ ሆኖ በመድረኩ ላይ ምክክር ተካሂዶበታል።

በውይይቱ ላይ የማህበረሰብ ራዲዮን ጨምሮ ከሁሉም የክልልና የፌደራል መገናኛ ብዙሃን የተውጣጡ ባለሙያዎች እየተሳተፉ ነው።

በመድረኩ ላይ የምርጫ አዘጋገብ፣ ስነ ምግባርና አሰራርን ለመደንገግ የወጣ መመሪያ ላይ ከዚህ ቀደም በተካሄደው ውይይት የተሰጡ የማሻሻያ ሃሳቦች ታክለውበት ውይይት ተደርጎበታል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.