Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ በምርጫ ሂደት  የሴቶችን ተሣትፎ ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥልጠና ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምርጫ ሂደት ውስጥ የሴቶችን ተሣትፎ ለማረጋገጥ የሚያስችል የሦስት ቀን  ሥልጠና ለምርጫ  ታዛቢዎች ሰጠ ።

በወቅቱም የቦርዱ አመራር የሆኑት ብዙወርቅ ከተተ ÷ የ6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ አካታች ለማድረግ  በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  እየተተገበሩ ያሉ ዘርፈ ብዙ ጥረቶች ላይ ማብራሪያ ሰጥተውበታል።

ምርጫን ለመታዘብ ሥርዓተ-ፆታ የሚያስፈልግባቸው ምክንያቶችና የሚካተቱበት አግባብነት፣ በምርጫው ሂደት ውስጥ በሁሉም ደረጃዎች ሥርዓተ-ፆታን ያማከለ የምርጫ መታዘብ፣ በምርጫ ሂደት ውስጥ የሴቶችን ተሣትፎ እና የፆታ እኩልንት የሚመለከት የሕግ ማዕቀፍ በኢትዮጵያ፣ በምርጫ ወቅት ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ዓይነት፣ በዓለም ዐቀፍና በሀገር ዐቀፍ ደረጃ የሴቶች ተሣትፎ እንቅፋቶች ሥልጠናው ካካተታቸው አጀንዳዎች ውስጥ እንደሚገኙበት ተገልጿል።

በሥልጠናው መጠናቀቂያ ላይ የቦርዱ የሥርዓተ-ፆታና ማኅበራዊ አካታችነት ክፍል ኃላፊ ለተሣታፊዎቹ የተሣትፎ የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል።

ሃላፊዋ ታዛቢዎቹ በምርጫው ሂደት ውስጥ የሚኖራቸው ተሣትፎ የሴቶችን እና ትኩረት የሚሹ ዜጎችን አካታችነት በሚያረጋግጥ መልኩ እንዲሆን ማሳሰባቸውን ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.