Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ 28 ተጨማሪ ንዑስ የምርጫ ጣቢያዎች መክፈቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች የምርጫ ጣቢያዎች 1 ሺህ 500 ሰው መዝግበው ምዝገባቸው በማለቁ ተጨማሪ 28 ንዑስ የምርጫ ጣቢያዎች መክፈቱን አስታወቀ።

ቦርዱ አዲስ የተከፈቱትን ተጨማሪ ንዑስ የምርጫ ጣቢያዎች አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፤

በአሁኑ ወቅት በስድስተኛው አጠቃላይ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በአብዛኛው የሃገሪቱ ክፍል የመራጮች ምዝገባ እየተከናወነ እንደሆነ ይታወቃል።

በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር እና በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች የምርጫ ጣቢያዎች 1500 ሰው መዝግበው መዝገባቸው ማለቁን ቦርዱ በሪፓርቱ ደርሶታል። በዚህም መሰረት ይህንን አጭር ማብራሪያ ያቀርባል።

1. በምርጫ አዋጁ 1162/2013 መሰረት አንድ ምርጫ ጣቢያ መመዝገብ የሚችለው 1500 ሰው ብቻ ሲሆን ይህም የሆነው በድምጽ መስጫ ቀን የሰው መጨናነቅን እና የዜጎች የመምረጥ መብትን ለማረጋገጥ ያለመ ነው።

2. አንድ የምርጫ ጣቢያ 1500 ሰው ሲሞላ የሚከተሉት እርምጃዎች ይወሰዳሉ

– አስፈጻሚዎች በተመሳሳይ ምርጫ ክልል እና በቅርብ ርቀት ያሉ የምርጫ ጣቢያዎችን በማጣራት መራጮች ካርድ የሚያገኙበትን ቦታ ይጠቁማሉ።

– የምርጫ ጣቢያው 1500 ሰው ከመዘገበ በኃላ መዝገቡን የሚዘጋ ሲሆን ሌላ ዙር 1500 መራጮች የሚመዘገቡት በአዲስ ንኡስ ምርጫ ጣቢያ ይሆናል።

ይህንንም ለማድረግ ተጨማሪ ቁሳቁስ የምርጫ ጣቢያ ኮድ እና የምርጫ አስፈጻሚችን ምደባ የሚጠይቅ ሲሆን ከድምጽ መስጫ ቀን በፊት ደግሞ ተጨማሪ ቢሮችን ማዘጋጀት የሚጠይቅ ይሆናል።

በዚህ መሰረት

ቦርዱ በዛሬው እለት አዲስ ንኡስ ጣቢያዎችን በመክፈት ቁሳቁስ ያሰራጨ ሲሆን ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች የተለመደ ትብብራቸውን በመስጠት ተጨማሪ ቢሮዎችን ለመክፈት ቦርዱን እንዲተባበሩት ይጠይቃል።

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ተጨማሪ የንኡስ ምርጫ ጣቢያ ተከፈተባቸው ቦታዎች

1. የምርጫ ክልል 19 ወረዳ 01 ምርጫ ጣቢያ 9_1 ንኡስ ጣቢያ

2. የምርጫ ክልል 19 ወረዳ 01 ምርጫ ጣቢያ 4 ንኡስ ጣቢያ

3. የምርጫ ክልል 19 ወረዳ 01 ምርጫ ጣቢያ 2 ንኡስ ጣቢያ

4. የምርጫ ክልል 19 ወረዳ 01 ምርጫ ጣቢያ 14 ንኡስ ጣቢያ

5. የምርጫ ክልል 19 ወረዳ 01 ምርጫ ጣቢያ 17 ንኡስ ጣቢያ

6. የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 12 ምርጫ ጣቢያ አባይ ንኡስ ጣቢያ

7. የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 12 ምርጫ ጣቢያ ካ.ቁ 4 ንኡስ ጣቢያ

8. የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 12 ምርጫ ጣቢያ ካ- ቁ.3 ንኡስ ጣቢያ

9. የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 12 ምርጫ ጣቢያ አባዶ -1 ንኡስ ጣቢያ

10. የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 13 ምርጫ ጣቢያ አያት ንኡስ ጣቢያ

11. የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 13 ምርጫ ጣቢያ ጣፎ -2 ንኡስ ጣቢያ

12. የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 13 ምርጫ ጣቢያ አያት ንኡስ ጣቢያ

13. የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 13 ምርጫ ጣቢያ ገብርኤል ቁ.1 ንኡስ ጣቢያ

14. የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 10 ምርጫ ጣቢያ መሪ 2ለ1 ንኡስ ጣቢያ

15. የምርጫ ክልል 28 ወረዳ 10 ምርጫ ጣቢያ መሪ 1ሀ ንኡስ ጣቢያ

በኦሮሚያ ክልል በተጨማሪ የተከፈቱ ንኡስ ምርጫ ጣቢያዎች

1. አቦምሳ-02 ምርጫ ጣቢያ ቁጥር-4 ንኡስ ጣቢያ

2. አቦምሳ 02 ቀበሌ አቦምሳ ቁጥር 1 ንኡስ ጣቢያ

3. አቦምሳ 02 ቀበሌ አቦምሳ ቁጥር 2 ንኡስ ጣቢያ

4. አቦምሳ -02 ምርጫ ጣቢያ ቁጥር-3 ንኡስ ጣቢያ

5. አቦምሳ -01 ምርጫ ጣቢያ ቁጥር-1 ንኡስ ጣቢያ

6. አቦምሳ -01 ምርጫ ጣቢያ ቁጥር-2 ንኡስ ጣቢያ

7. አቦምሳ-01 ምርጫ ጣቢያ ቁጥር-3 ንኡስ ጣቢያ

8. በሌ 01 ምርጫ ጣቢያ በሌ 01 -ሀ ንኡስ ጣቢያ

9. በሌ 01 ምርጫ ጣቢያ በሌ 01 -ለ ንኡስ ጣቢያ

10. እተያ ምርጫ ጣቢያ እተያ ንኡስ ጣቢያ

11. ሲርማ ምርጫ ጣቢያ ሲርማ 1 “”ሀ”” ንኡስ ጣቢያ

12. መልካ አማና ምርጫ ጣቢያ ለ ንኡስ ጣቢያ

13. መና-02 ምርጫ ጣቢያ 02-ለ ንኡስ ጣቢያ

ሲሆኑ በተጨማሪ ይህንኑ ተመሳሳይ ሂደት በመከተል አስፈላጊ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ ተጨማሪ ንኡስ የምርጫ ጣቢያዎችን እንደሚከፍት ለመግለጽ እንወዳለን።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.