Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ በኦብነግ አመራሮች መካከል ያለውን አለመግባባት አስመልክቶ የቀረቡትን ሰነዶች በመመርመር ውሳኔ ማስተላለፉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻነት ግንባር (ኦብነግ)ን አስመልክቶ ውሳኔ አስተላለፈ::
በእነ አቶ ራያል ሃሙድ በኩል ከጥር 12-15 ቀን 2013 ዓ.ም. ተካሂዷል የተባለው አስቸኳይ የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ስለመጠራቱ የሚያሳይ ሰነድ ያልቀረበ መሆኑን ምርጫ ቦርድ በውሳኔው አስታውሷል፡፡
በአስቸኳይ ስብሰባው ላይ ተገኙ ከተባሉት 47 ሰዎች መሃል 10 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ብቻ በመሆናቸው በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀፅ 11.2 እና በአንቀፅ 13.1 መሠረት ምልአተ ጉባኤ ሳይሟላ የተካሄደ ስብሰባ መሆኑንም አንስቷል፡፡
በእለቱ የተካሄደውን ስብሰባ የመሩትና የፓርቲው “ምክትል ሊቀመንበር” እንደሆኑ የተገለፁት አቶ ራያል ሃሙድ በቦርዱ ጽሕፈት ቤት በሚገኘው የፓርቲው ሰነድ ላይ የሚታወቁት በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ሲሆን የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አቶ አህመድ ያሲን ሼክ ኢብራሂም መሆናቸውን አስታውቋል፡፡
የፓርቲው ሊቀመንበር የፈፀሟቸው ጉዳዮች በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀፅ 33 መሠረት በዲስፕሊን ኮሚቴ ስለመታየታቸው የቀረበ ሰነድ ያለመኖሩንም ነው ቦርዱ የገለፀው፡፡
በዕለቱ በተካሄደው ስብሰባ አስራ አምስት “የሽግግር ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ” እና ሶስት የውስጥ ኦዲት መመረጡን መግለፁ ስብሰባው ምልአተ ጉባኤ ሳይሟላ የተካሄደ ከመሆኑ በተጨማሪ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ስለ “ሽግግር ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ” የተደነገገ እንደሌለም ነው ምርጫ ቦርድ በውሳኔው የገለፀው፡፡
በአራት ወራት ውስጥ ብሔራዊ ጉባኤ እንዲካሄድ የተላለፈው ውሣኔ ምልአተ ጉባኤ ሳይሟላ የተካሄደ ከመሆኑ በተጨማሪ ከመተዳደሪያ ደንቡ አንቀፅ 10.3 እና አንቀፅ 12.7 ጋር የሚቃረን በመሆኑ፣ ቦርዱ ከላይ የተገለፁት በፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባ ተላልፈዋል የተባሉት ውሣኔዎች በሙሉ ተቀባይነት የላቸውም ሲል ወስኗል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በፓርቲው ሊቀመንበር በኩል በፓርቲው ስነምግባር ደንብ መሠረት ክስ ቀርቦ በዲሲፕሊን ኮሚቴው ከተገመገመና ከተጣራ በኋላ 22 ሰዎች እንዲባረሩ 7 ሰዎች ለ6 ወራት እንዲታገዱ ስለመወሰኑ የተገለፀው ተጠቃሾቹ የተከሰሱበትን ጉዳይም ሆነ አጠቃላይ ሂደቱን የሚያሳይ ቃለጉባኤና ተያያዥ ሰነዶች ያልቀረቡ በመሆኑ ቦርዱ ውሣኔው ተቀባይነት የለውም ሲል የወሰነ መሆኑን ቦርዱ ያሳውቃል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.