Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ ኮቪድ19 በምርጫው ሂደት ላይ በሚኖረው ተፅዕኖ እና የመከላከያ መንገዶች ላይ ከፓርቲዎች ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ኮቪድ19 በምርጫው ሂደት ላይ በሚኖረው ተፅዕኖ እና የመከላከያ መንገዶች ላይ ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
 
ፓርቲዎቹ በመጭው ሃገራዊ ምርጫ ዙሪያ ማማከር፣ በምርጫው ያላቸውን ግብዓትና አስተያየታቸውን መቀበልም የምክክሩ አካል ነው ተብሏል፡፡
 
በተጨማሪም ኮቪድ19 በምርጫ ትግበራ ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ፣ አሰራር እና የመመሪያ አቅጣጫዎች ማስቀመጥ ላይም ያተኮረ ውይይት ነበር፡፡
 
በውይይቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመጭው ሃገር አቀፍ ምርጫ ዙሪያ ያላቸውን አስተያየት አቅርበዋል፡፡
 
የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተሳተፉበት ውይይት የምርጫ ፀጥታ እና የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ዝግጅት ለፓርቲዎቹ ቀርቧል።
 
ቦርዱ የምርጫ ዋና ዋና ተግባራ እና የሚከናወንበትን ጊዜ በተመለከተም ገለጻ አድርጓል።
 
በለይኩን ዓለም
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.