Fana: At a Speed of Life!

ቦይንግ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ገብቶ የማምረት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቦይንግ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ገብቶ የማምረት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ፡፡

ከቦይንግ ኩባንያ፣ ከስካይ ቴክኖ ኩባንያ እንዲሁም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተወጣጡ የስራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች በአዲስ አበባ የሚገኙ የቦሌ ለሚ፣ የቂሊንጦ እና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፓርኮችን ጎብኝተዋል፡፡

በጉብኝቱ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ሰለሞንን ጨምሮ የቦሌ ለሚ፣ ቂሊንጦ እና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ ስራ አስኪያጆች ተሳትፈዋል፡፡

በጉብኝቱ በሶስቱ ፓርኮች ውስጥ ያሉ ምቹ የኢንቨስትመንት አማራጮች ለጎብኚዎቹ በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን÷በየፓርኮቹ ውስጥ ያሉ መሰረተ ልማቶችን፣ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሺንትስ የተሰኘው ኩባንያን የምርት ሂደት እና የተመረቱ ምርቶችን መጎብኘታቸውን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ጎብኝዎቹ በተመለከቷቸው ዝርዝር የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመሳተፍና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ መስራት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ ጋር የአውሮፕላን ውስጥ የኤሌክትሪክ ገመዶችን እንዲሁም ሌሎች እቃዎችን እያመረተ ለማቅረብ የተስማማ ሲሆን÷ኩባንያውም በኢንዲስትሪ ፓርኮች ውስጥ ገብቶ የአውሮፕላን እቃዎችን እንዲያመርት ጥረት እንደሚያደርግ ሀላፊዎቹ ገልፀዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.