Fana: At a Speed of Life!

ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን የሙከራ በረራ ሊያደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን የሙከራ በረራ ሊያደርግ መሆኑ ተሰማ፡፡

አውሮፕላኑ ከዛሬ ጀምሮ ለቀጣይ ሶስት ቀናት የሙከራ በረራውን እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡

ነገር ግን የዚህ የሙከራ በረራ ስኬታማነት ማክስ 737 ወደ ገበያ የመመለስ ዋስትናን አይሰጠውም ነው የተባለው።

አውሮፕላኑ ወደ ገበያ ለመመለስ ሌሎች ፈተናዎችን ማለፍ ይጠበቅበታል ተብሏል።

የቦይንግ ምርት በሆኑት 737 ማክስ አውሮፕላኖች በኢትዮጵያ እና በኢንዶኔዢያ በደረሰ አደጋ በድምሩ የ346 ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትትሎ ካሳለፍነው ዓመት መጋቢት ወር ጀምሮ አውሮፕላኖቹ በረራ ማቆማቸው ይታወሳል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ
#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.