Fana: At a Speed of Life!

ተለዋጭ የዓባይ ወንዝ ድልድይ ግንባታ 41 ነጥብ 1 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 1፣2014 (ኤፍ ቢሲ)እየተገነባ የሚገኘውን ተለዋጭ የዓባይ ወንዝ ድልድይ ግንባታ የስራ ሂደት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለና የሥራ ኀላፊዎች ጎብኝተዋል፡፡

በባሕር ዳር ከተማ እየተገነባ የሚገኘው ይህ ተለዋጭ የዓባይ ድልድይ በቻይና ኮንስትራክሽን ኮምዩኒኬሽን ካምፓኒ ነው ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው፡፡

በ2011 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረው ተለዋጭ የዓባይ ድልድይ 43 ሜትር ስፋት እና 380 ሜትር ርዝመት እንዳለው አሚኮ ዘግቧል፡፡

ግንባታው በአሁኑ ወቅት 69 ነጥብ 1 በመቶ መድረስ የነበረበት ቢሆንም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ፣ የወሰን ማስከበር ችግር እና የግንባታ ቁሳቁስ እጥረት በዕቅዱ መሰረት እንዳሄድ እንዳደረገው ተጠቅሷል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.