Fana: At a Speed of Life!

ተመስጦ ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊትን ለመቀነስ ያስችላል – ጥናት

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)ተመስጦ ወይም ራስን ማዳመጥ ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊትን ለመቀነስ እንደሚያሰችል አንድ አዲስ ጥናት አመላክቷል።

ጥንቃቄ የተሞላበት ተመስጦ ወይም አዘውትሮ ውስጣዊ ስሜትን ማዳመጥ ከፍተኛ የደም ግፊትን ለመቀነስ የሚያስችል መሆኑን የጥናቱ ተመራማሪዎች ተናግረዋል።

በዚህም ደም ግፊት ለመቀነስ ጥናት ለማድረግ በተደረገ መርሃ ግብር የተመዘገቡ ተሳታፊዎች ከሙከራው 1 ዓመት በኋላ የደም ግፊት መጠናቸው በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል፡፡

በጥናቱ መሰረት ለውጥ ሊመጣ የቻለው ከተመስጦ ባሻገር ተሳታፊዎች የህይወት ዘይቤያቸውን በማሻሻል እንዲሁም በሃኪም የታዘዙላቸውን መድሃኒቶች እንዲወስዱ መደረጋቸው ነው ተብሏል፡፡

የደም ግፊት በሽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሞት መንስኤ ከመሆኑም ባሻገር ለልብ ህመም ያጋልጣል፡፡

ደም ግፊትን ለመቀነስ አመጋገባችንን ማስተካከል ማለትም የጨው መጠንን መቀነስ፣ መደበኛ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ እንዲሁም ክብደት መቀነስ እንደሚገባ ይመከራል፡፡

ሆኖም አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ዓይነቱን ዘላቂ የአኗኗር ዘይቤ መከተል አስቸጋሪ ሆኖ ይሰማቸዋል፡፡

ይህም ለሐኪሞችም ሆነ ለታማሚዎች የደም ግፊት ህመምን መቀነስ ፈታኝ ያደርገዋል ነው የተባለው።

ምንጭ፡-medical news today

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.