Fana: At a Speed of Life!

ተመድ ሶማሊያ የዘገየውን ምርጫ በፍጥነት እንድታካሂድ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 16 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተመድ የሶማሊያ ልዩ ልዑክ ጀምስ ስዋን የሶማሊያ መሪዎች “ከመጋጨት ወደ ኋላ እንዲመለሱ” እና በምርጫዎች ላይ ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ጥሪ አቅርበዋል።

ሃላፊው ጥሪውን ያቀረቡት በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ በተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ ወቅት የተኩስ ልውውጥ ከተካሄደ ከቀናት በኋላ  መሆኑ ተመላክቷል።

ሁሉም የሶማሊያ የፖለቲካ መሪዎች ከተፈጠረው ግጭት ወደ ኋላ እንዲመለሱ እና አደገኛ የአሸናፊነት-ተኮር ስልቶችን ሁሉ እንዲያስወግዱ አሳስበዋል ፡፡

አያይዘውም በፈረንጆቹ መስከረም 17 ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ እና በክልል መሪዎች    የተደረሰውን ስምምነት መነሻ በማድረግ ምርጫን በተቻለ ፍጥነት ለማካሄድ ሁሉን አቀፍ እና ተዓማኒ የፖለቲካ ስምምነት ላይ ለመድረስ ውይይትን እና ድርድርን ማድረጊያ ጊዜው አሁን ነው ብለዋል ፡፡

ሀገሪቷ የካቲት 8 ድረስ ምርጫ ለማካሄድ  ቀነ-ገደብ ብታስቀምጥም ያንን ማሳካት አልተቻለም፡፡

በዚህም የተቃዋሚ እጩዎች ጥምረት ከአሁን በኋላ ፋርማጆን እንደ ፕሬዚዳንት እንደማይቀበሉ በመግለጽ ስልጣናቸውን እስከሚለቁ ድረስ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞው እንደሚቀጥል  ነው የሚናገሩት።

ምንጭ፡-አልጀዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.