Fana: At a Speed of Life!

ተመድ የሊቢያ ተቀናቃኝ ኃይሎች ዘላቂነት ያለው የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሊቢያ ተቀናቃኝ ኃይሎች ዘላቂነት ያለው የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

ተቀናቃኝ ኃይሎቹ ጄኔቫ ተገናኝተው ስምምነቱን መፈረማቸው ተሰምቷል፡፡

ተመድ ታሪካዊ ነው ባለው በዚህ ስምምነት የተኩስ አቁሙ በሁሉም የሀገሪቱ ግዛቶች ተፈጻሚነት እንደሚኖረው ገልጿል፡፡

ስምምነቱ በጦርነቱ ውስጥ እየተሳተፉ የሚገኙ ቅጥረኛ ተዋጊዎችና የውጭ ኃይሎች በሦስት ወራት ውስጥ ሊቢያን ለቀው እንደሚወጡም ያትታል፡፡

ከዚህ ቀደም ሁለቱ ተቀናቃኝ ኃይሎች ስምምነት የደረሱበትን የተኩስ አቁም መጣሳቸው የሚታወስ ነው፡፡

ይህ ስምምነት የሚጸና ከሆነ ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ በእርስ በርስ ጦርነቱ እየማቀቁ ለሚገኙ ዜጎች ትልቅ ተስፋ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.