Fana: At a Speed of Life!

ተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ ፓርኮችን ግንባታ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ሽግግርና ለስራ እድል ፈጠራ ከፍተኛ አስተዋዕኦ ያላቸውና በመገንባት ላይ የሚገኙ የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፓርኮችን ወደ ምርት ሂደት ለማስገባት በትኩረት እተሰራ መሆኑን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአግሮ – ኢንዱስትሪ ፓርክና የኢንዱስትሪ ልማት ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አያልነህ አባዋ በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች እየተገነቡ የሚገኙት የተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ ፓርኮችን ወደ ምርት ሂደት ለማስገባት በእውቀት፣ በገንዘብና በልዩልዩ የአቅም ግንባታ ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
የፓርኮቹ ግንባታ የብዙ አካላትን ቅንጅት የሚፈልግ በመሆኑ ከግብርና፣ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ ከመብራት ኃይል፣ ከኢትዮ-ቴሌኮም፣ ከምግብና መድኃኒት እና ከተስማሚነትና ምዘና ድርጅት የተውጣጣ ብሔራዊ ስትሪግ ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራው በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡
በይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፓርክ 11 ሸዶች የተገነቡ ሲሆን አራቱ ስራ መጀመራቸውን የፓርኩ የኦፕሬሽንና አስተዳደር ስራ አስኪያጅ አቶ ግዛቸው ሻላ ተናግረዋል፡፡
አቶ ግዛቸው እንደገለጹት የውሃ፣ የመብራት እና የመንገድ ስራዎች 85 በመቶ የተጠናቀቁ ሲሆን የደረጃ አንድ (ፌዝ አንድ) ግንባታ ተጠናቋል፡፡
በፓርኩ ግንባታ ምክንያት ከይዞታቸው የተነሱትን የአካባቢው ማህበረሰቦች ተጠቃሚ ለማድረግ አንድ የህፃናት ማቆያ ተገንብቶ ስራ መጀመሩንና 100 ህፃናትን ተቀብሎ በነፃ እያስተማረ እንደሚገኝ አቶ ግዛቸው ጠቁመዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.