Fana: At a Speed of Life!

ተቃውሞ የበረታባቸው የቤላሩሱ ፕሬዚዳንት ሉካሼንኮ ከ ፑቲን ጋር ለመምከር ወደ ሩሲያ አቅንተዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4 2013 (ኤፍ..) ተቃውሞ የበረታባቸው የቤላሩሱ ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ከሩስያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለመምከር ወደ ሶቺ አቅንተዋል።

ሉካሼንኮ አገራቸው ከአንድ ወር በፊት ያደረገችውን ምርጫ ተከትሎ ተቃውሞ በርትቶባቸዋል።

በምርጫው ሉካሼንኮ ማሸነፋቸው የሚታወስ ሲሆን፥ የተቃዋሚ አመራሯ ወደ ጎረቤት ሀገር ተሰደዋል።

በትናንትናው ዕለት ብቻ በዋና ከተማዋ ሚኒስክ 100 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች ለተቃውሞ አደባባይ መውጣታቸው ተነግሯል።

የሁለቱ መሪዎች ውይይት ስትራቴጂካዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር የተነገረ ሲሆን፥  በኃይል፣ በንግድ እንዲሁም ባህላዊ ባሏቸው ፕሮጀክቶች ላይ እንደሚመክሩ ይፋ አድርገዋል፡፡

በምዕራባውያን እየተገፉ የመጡት 65 ዓመቱ ሉካሼንኮቭ ወደ ሩስያ ያቀኑት የፑቲንን ድጋፍ ለማግኘት ነው ተብሏል።

ፕሬዚዳንት ሉካሼንኮቭ በምስራቅ አውሮፓ የምትገኘው ቤላሩስን 26 ዓመታት መርተዋል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.