Fana: At a Speed of Life!

ተቋርጦ የቆየው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የቫይረሱን ስርጭትን ከግምት ባስገባ መልኩ ወደ ተግባር እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ወደ ተግባር ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ።:
የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራምን አስመልክቶ አዲስ ለተቋቋመው አስፈፃሚ ግብረ ሀይል ስልጠና ተሰጥቷል።
ስልጠናዉን የከፈቱት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሰላም ግንባታ ዳይሬክተር ጀነራል ወይዘሮ አስማ ረዲ የሰላም ሚኒስቴር በጎ ፈቃደኝነትን ለሰላምና ለብሔራዊ መግባባት ለማዋል ሰፊ ስራ እየሰራ ነው ብለዋል ።
”የወጣት በጎ ፈቃደኝነት ለነፃ አስተሳሰብ እና ሀገራዊ ብልፅግና ” በሚል መሪ ሃሳብ በመላ ሀገሪቱ የሚተገበረው የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ስብዕና ግንባታ፣ ሀገራዊ አብሮነትን ማጠናከር፣ ማህበራዊ ትስስርን ማጎልበትና ሰላም ግንባታ ላይ ትኩረት ያደርጋል ነው ያሉት ።
የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም በቅርቡ በመላ ሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ከግምት ባስገባ መልኩ ቅድመ-ዝግጅት በማድረግ ወደ ተግባር ይገባል ተብሏል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.