Fana: At a Speed of Life!

ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ መደበኛ አገልግሎት መመለሱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ዛሬ በአብዛኛው የሃገሪቱ ክፍል ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ሃይል ወደ መደበኛ አገልግሎት መመለሱን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ የተከሰተው ከጣና በለስ ወደ ባህርዳር የሚሄድ 400 ኪሎ ቮልት የሚሸከም የኃይል መስመር ላይ ባጋጠመ የቴክኒክ ችግር ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሆኖም አሁን ላይ ችግሩን በአፋጣኝ ለመቅረፍ በተሰሩ ስራዎች የኤሌክትሪክ ኃይል የተቋረጠባቸው ሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸውን ገልፀዋል፡፡
መሰል ችግሮች በብዛት የሚከሰቱ አይደሉም ያሉት ዳይሬክተሩ ከተከሰቱ ግን በአፋጣኝ ችግሩን መፍታት ላይ ትኩረት ደረጋል ብለዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.