Fana: At a Speed of Life!

ተዘዋዋሪ ችሎቱ በ27 ሰዎች ሞት ከተከሰሱት መካከል በዘጠኙ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ

 

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሶሳ እና አካባቢው አንደኛ ተዘዋዋሪ ችሎት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን በ27 ሰዎች ሞት ክስ ከተመሰረተባቸው 48 ሰዎች መካከል በዘጠኙ ላይ ከ8 እስከ 21 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑ ተገለጸ፡፡

ከሳሹ በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጸው፤ ከመስከረም 17 እስከ ህዳር ወር መጨረሻ 2011 ዓ.ም በክልሉ ካማሽ ዞን “አጋሎሜጢ ወረዳ” እና አጎራባች አሮሚያ ክልል አካባቢዎች ተከስቶ በነበረ ግጭት የ27 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡

በግጭቱ በርካታ ሰዎች የአካል ጎዳት ሲደርስባቸው ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎችም ከቄያቸው መፈናቀላቸውን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ አስታውሷል፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በእነገመቹ ጉተማ የክስ መዝገብ በተዘረዘሩ 15 ክሶች የእርስ በርስ ግጭት  በማስነሳት እና በመሳተፍ እንዲሁም በከባድ የግድያ ወንጀል በ48 ሰዎች ላይ ክስ መመስረቱ ተመልክቷል፡፡

በዚህም በማረሚያ ቤት ቆይተው  ቀረበባቸውን ይህንኑ የወንጀል ክስ መከላከል ያልቻሉ ዘጠኝ ተከሳሾች የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሶሳ እና አካባቢው አንደኛ ተዘዋዋሪ ችሎት ጉዳያቸውን በመመልከት የቅጣት ወሳኔ ማስተላለፉን  የጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ አስታውቋል።

ዘርፉ እንዳመለከተው፥ ተዘዋዋሪ ችሎቱ ታህሳስ 15 ቀን 2014 ዓ.ም በአሶሳ ከተማ በዋለው ችሎት ተከሳሾቹ ከስምንት እስከ 21 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ችሎቱ ወስኖባቸዋል።

በዚህም መሠረት ችሎቱ 40ኛ ተከሳሽ ተሊንቲ ሙለታ ኩምሳ፣ 41ኛ ተከሳሽ በሊና ቦረና ሃጂን እና 42ኛ ተከሳሽ ሰንበታ ጉደታ ዲቢሳ  እያንዳንዳቸው ላይ የ21 ዓመት ጽኑ እስራት የቅጣት ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል፡፡

18ኛ ተከሳሽ ታፈሰ መርጋ ጢሎ፣ 24ኛ ተከሳሽ ንብረት ገለታ ቤዶ፣ 32ኛ ተከሳሽ ጸጋ ታዬ ሲዳ፣ 36ኛ ተከሳሽ አመንቴ እሬሳ ከሚሰ እና 44ኛ ተከሳሽ ዳንኤል ቡሽራ ኩሜ እያንዳንዳቸው በዘጠኝ ዓመት እንዲሁም 39ኛ ተከሳሽ አድማሱ ፋራ ዋልተጂ  በስምንት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ የተወሰነባቸው መሆኑ ተመልክቷል።

በፖሊስ ተፈልገው ያልተገኙ ቀሪ ተከሳሾች የክስ መዝገብ ለጊዜው ተቋርጦ ተፈልገው በሚቀርቡበት ወቅት ጉዳያቸው እንደገና እንዲታይ ተዘዋዋሪ ችሎቱ መወሰኑን የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ አስታውቋል፡፡

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.