Fana: At a Speed of Life!

ተጠሪነታቸው ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሆኑት ዩኒቨርስቲዎች ከ91 ሚሊየን ብር በላይ ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አበረከቱ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 13 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ተጠሪነታቸው ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሆኑት ዩኒቨርስቲዎች ከ91 ሚሊየን ብር በላይ ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አበርክተዋል።

ከዚያም ባለፈ ዩኒቨርስቲዎቹ በጎርፍ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖችም ከ14 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል።

ከመስከረም 10 ጀምሮ ለ 3 ቀናት በጅማ ዩኒቨርስቲ መሰብቢያ አዳራሽ ሲካሄድ የነበረው የከፍተኛ ትምህርት ማስቀጠያ ቅድመ ዝግጅት እና የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምላሽ ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ ተጠናቋል።

በማጠቃለያው ውይይት ዩኒቨርስቲዎቹ ለገበታ ለሀገር ፕሮጀክት 91 ነጥብ 3 ሚሊየን በገንዘብ፣24 ሚሊየን በአይነትና በሙያ እንዲሁም በጎርፍ ለተጎዱ ወገኖች 14 ነጥብ 35 ሚሊየን ብር በገንዘብ እና 1 ነጥብ 1 ሚሊየን በአይነት ለማበርከት ቃል ገብተዋል።

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በድጋፉ ተሳትፎ ያደረጉት 32 ዩኒቨርስቲዎች መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የገበታ ለሀገር ጎርጎራ፣ ወንጪ እና ኮይሻን በማልማት የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ ያለመ ፕሮጀክት ነው።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.