Fana: At a Speed of Life!

ተጠቃሚዎች የመድሃኒትን ህጋዊነት የሚያረጋግጡበት የሞባይል መተግበሪያ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ከአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ ኤይድ) ጋር በመተባበር ተጠቃሚዎች የመድሃኒትን ህጋዊነት የሚያረጋግጡበት የሞባይል መተግበሪያ ይፋ አደረገ፡፡

መተግበሪያው አይ ቨሪፋይ (i. verify) የተሰኘ ሲሆን በኢንተርኔት የሚሰራ ነው ተብሏል፡፡

አዲሱ መተግበሪያ i- license፣ i- register እና i- import ከተባሉ መተግበሪያዎች ቀጥሎ የመጣ መሆኑም በመድረኩ ተገልጿል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሳህረላህ አብዱላሂ ይህንን መተግበሪያ የሞባይል ተጠቃሚዎች በቀላሉ የመድሃኒቱን ደህንነት ማረጋገጥ እንዲችሉ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ዳይሬክተር ጀነራል ወይዘሪት ሄራን ገርባ በበኩላቸው ከስድስቱ መሰረታዊ የጤና ስርአት ምሰሶዎች አንዱ የጤና ግብዓት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

የግብአቱን ጥራት ፈዋሽነትና ደህንነት ለማስጠበቅም ህብረተሰቡ የቁጥጥሩ ስርአት ባለቤት እንዲሆን የተቀመጠውን አቅጣጫ ለማገዝ የሚያስችል የቴክኖሎጂ ስርአት እንደሆነ መናገራቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.