Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 1 ሺህ 472 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ14 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ለ18 ሺህ 851 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1 ሺህ 472 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡

ከዚህ ባለፈም ባለፉት 24 ሰአታት የ14 ሰዎች ህይወት ማለፉንም አስታውቀዋል፡፡

አሁን ላይ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 692 ደርሷል፡፡

በተጨማሪም ባለፉት 24 ሰአታት 267 ሰዎች ሲያገግሙ ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 15 ሺህ 262 ደርሷል፡፡

275 ሰዎች ደግሞ በፅኑ ህክምና ክፍል ይገኛሉም ነው የተባለው፡፡

በኢትዮጵያ እስካሁን ለ775 ሺህ 908 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 42 ሺህ 143 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ከዚህ ውስጥ 15 ሺህ 262ቱ ሲያገግሙ 26 ሺህ 187 ሰዎች ደግሞ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.