Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 359 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 953 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 23፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ5 ሺህ 726 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 359 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሯ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ 353 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም 953 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 54 ሺህ 405 ደርሷል፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት የ11 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም 1 ሺህ 489 መድረሱን ገልጸዋል፡፡
ወረርሽኙ ኢትዮጵያ መግባቱ ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ ለ1 ሚሊየን 492 ሺህ 996 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተካሄደ ሲሆን 96 ሺህ 942 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.