Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 364 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 607 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ለ4 ሺህ 628 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 364 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡
 
ሚኒስትሯ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ 314 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም 607 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 48 ሺህ 150 ደርሷል፡፡
 
ባለፉት 24 ሰዓታት የ11 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም 1 ሺህ 437 መድረሱን ገልጸዋል፡፡
 
ወረርሽኙ ኢትዮጵያ መግባቱ ከተሰማበት ጊዜ ጀምሮ ለ1 ሚሊየን 449 ሺህ 170 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ የተካሄደ ሲሆን 93 ሺህ 707 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.