Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 408 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5 ሺህ 547 የላቦራቶሪ ምርመራ 243 ሰዎች ኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 124 ሺህ 264 ደርሷል።

በትናንትናው ዕለት 226 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 112 ሺህ 96 ሆኗል።

ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮናቫይረስ ሳቢያ የአምስት ሰዎች ህይወት አልፏል።

ይህንን ተከትሎም ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 923 ደርሷል።

በአሁኑ ወቅት ቫይረሱ ካለባቸው 10 ሺህ 243 ሰዎች መካከል 234 ያህሉ በጽኑ ሕክምና ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ እስካዛሬ ድረስ በአጠቃላይ ለ1 ሚሊየን 800 ሺህ 236 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅ ታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.