Fana: At a Speed of Life!

ተጫዋቾችን ለማዘዋወር የተቀመጠው የደመወዝ ጣሪያ እንዲነሳ ተወሰነ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ))የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የሊጉን ተሳታፊ ክለቦች ተጫዎቾች ለማዘዋወር የተቀመጠው 50 ሺህ ብር የደመወዝ ጣሪያ ገደብ እንዲነሳ ወሰነ።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ያካሄደ ሲሆን የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ተጫዎቾችን ለማዘዋወር የተቀመጠው 50 ሺህ ብር የደመዝ ጣሪያ ገደብ ዙሪያ፣ የዳኞችና ኮሚሽነሮች የውሎ አበል ማሻሻያ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
የአክሲዮን ማኅበሩ የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ የተጫዋች የደመወዝ ጣሪያ መቀመጡ ከጅምሩም ህገወጥ መሆኑንና ክለቦችንም ለተለያዩ ችግሮች መዳረጉን መስታወሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በአገሪቷ የተጫዋቾች ዝውውር ፕሮፌሽናል አካሄድ እንዳይኖረው በማድረግና በተጫዋቾችና ክለቦች መካከል በየጊዜው አለመግባባት እንዲፈጠር በማድረግ ውድድሩ ላይ ተፅእኖ ማሳደሩንም አንስተዋል።
በክለቦችም በኩልም መመሪያ መቀመጡ ህገወጥ ከመሆኑ በተጨማሪ በአብዛኞቹ ክለቦች በትክክል ተግባራዊ እየተደረገ አለመሆኑን ጠቁመው በአብዛኞቹ ክለቦች በመመሪያ የተቀመጠውን የደመወዝ መጠን የውል ወረቀት ላይ እንጂ በውስጥ ተጨማሪ ገንዘብ ለመክፈል ድርድሮች መኖራቸውን ነው የተናገሩት።
ይህም የተጫዋቾች የደመወዝ ጣሪያ ከእግር ኳሱ እድገት በላይ እንዳይሆን ታስቦ የወጣውን ዓላማ ከማሳካት ይልቅ መንግስት ማግኘት ያለበትን ግብር እንዲያጣ አድርጓል ያሉ ሲሆን ችግሩን ለመፍታት በቀጣይ ተጫዋቾችን እንደ አቅማችው የደመወዝ ገደብ ሳይደረግባቸው እንዲያስፈርሙ ውሳኔ ተላልፏል።
በጉባኤው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ከሌላው ዓመት በተለየ የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት እንዲያገኝ በመደረጉና ስያሜው በመሸጡ ከዲ.ኤስ.ቲቪ ከተገኘውን 4 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ክለቦች የሚያገኙት የገንዘብ መጠንም ይፋ ሆኗል።
ከተገኘው 4 ሚሊዮን ዶላር ገቢ 60 በመቶ ያህሉን ሁሉም ክለቦች እኩል የሚካፈሉ ሲሆን 25 በመቶውን ደግም እንደየውጤታቸው ቅደም ተከተል ይደርሳቸዋል ነው የተባለው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.