Fana: At a Speed of Life!

ተፈናቃይ ተማሪዎችን በሁሉም ዞኖች ለማስተማር ጥረት እየተደረገ መሆኑን የአማራ ክልል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ተፈናቃይ ተማሪዎችን በሁሉም የክልሉ ዞኖች ለማስተማር ጥረት እየተደረገ መሆኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
የትምህርት ቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሙላው አበበ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት አስተያየት፥ የ2014 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ከመጀመሩ አስቀድሞ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል።
በክልሉ ከየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ከተወሰኑ ዞኖች፣ ማለትም ደሴ ከተማ አስተዳደር፣ ሰሜን ጎንደርና እብናት አካባቢዎች በስተቀር መስከረም 24 በሁሉም ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች ትምህርት መጀመሩን ተናግረዋል።
እንደ ምክትል ኃላፊው ገለፃ የምስራቅ ጎጃም አስተዳደርና የትምህርት አመራር በአሸባሪውና ወራሪው ትህነግ ቡድን ምክንያት ከቤት ንብረታቸውና ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው ወደ ዞኑ የሚመጡ ተፈናቃዮችን ተቀብሎ ለማስተማርና ድጋፍ ለማድረግ በወሰደው አቅጣጫ ተማሪዎችን በግል ትምህርት ቤቶች ሳይቀር ተቀብሎ ለማስተማር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።
የተፈናቃይ ተማሪዎችን በተመለከተ የክልሉ መንግሥትና ትምህርት ቢሮው ባስቀመጠው አቅጣጫ በሁለት መንገድ እየተስተናገዱ ነው ያሉት አቶ ሙላው፥ ተፈናቃይ ተማሪዎች ለመማር ፈልገው ሲመጡ ማንኛውም ትምህርት ቤት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲያስተናግድ ማድረግ የመጀመሪያው ስልት ነው ብለዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person, fire and text
0
People Reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.