Fana: At a Speed of Life!

ተፈናቃይ የነበሩ የሰሜን ወሎ ዞን ወጣቶች ወታደራዊ ስልጠናዎችን ወስደው ጥምር ጦሩን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ተፈናቃይ የነበሩ እና ብሶት የወለዳቸው የሰሜን ወሎ ዞን ወጣቶች የተለያዩ ወታደራዊ ስልጠናዎችን ወስደው ጥምር ጦሩን ተቀላቀሉ።
አሸባሪው ህወሓት በአማራ ክልል ወረራ ከፈፀመባቸው እና በርካታ ሰብዓዊ ጥቃት ካደረሰባቸው አካባቢዎች የሰሜን ወሎ ዞን አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ላለፉት አራት እና አምስት ወራት በሽብር ቡድኑ ወረራ ምክንያት ቤተሰቦቻቸው ተገድለዋል፣ ሴቶች ተደፍረዋል፣ ነዋሪዎችም ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል እንዲሁም ይገለገሉባቸው የነበሩ መሰረተ ልማቶችም ወድመዋል።
ይህን ተከትሎ ከሰሜን ወሎ ዞን ሰባት ከሚሆኑ ወረዳዎች በዘንዘልማ የስደተኞች መጠለያ የነበሩ ብሶት የወለዳቸው ወጣቶች የተለያዩ ወታደራዊ ስልጠናዎችን ወስደው የሽብር ቡድኑን ለመውጋት መዘጋጀታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
ሰልጣኞቹ በሰሜን ወሎ የላስታ ላሊበላ የፋኖ ክንፍ በሚል በወታደራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ስልጠናዎች ተሰጥቷቸዋል።
ሰልጣኞቹ የአማራን ህዝብ በማዳከም ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሰራ የሚገኘውን የህወሓት የሽብር ቡድን እስከመጨረሻው እንታገላለን ብለዋል፡፡
በምንይችል እዘዘው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.