Fana: At a Speed of Life!

ቱርክ ከፈረንጆች 2023 ጀምሮ በጥቁር ባሕር በኩል በየቀኑ 10 ሚሊየን ሜትር ኪዩቢክ የተፈጥሮ ጋዝ ልታስገባ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቱርክ ከፈረንጆች 2023 የመጀመሪያ ሩብ አመት ጀምሮ በየቀኑ 10 ሚሊየን ኪዩቢክ ሜትር የተፈጥሮ ጋዝ ከጥቁር ባህር ሳካሪያ የጋዝ ማመንጫ ስፍራ ወደ ብሄራዊ የጋዝ ማስተላለፊያ መስመር እንደምታስገባ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶኻን ገለጹ፡፡
በሳካሪያ ጋዝ ማመንጫ ስፍራ የሚገኘው የጋዝ ምርት በ2026 መጠኑ ከፍ እንደሚል ተስፋ እናደርጋለን ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን፡፡
የማስተላለፍ ስራው እና ሌሎች መሰል ስራዎች በሀገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ እንደሚሰራ ጠቅሰው፥ ይህም ከፍተኛ አድናቆት የሚቸረው ነው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡
የመጀመሪያው የጋዝ ማስተላለፊያ በ150 ኪሎ ሜትር ርዝመት ባለው የባሕር ውስጥ ቧንቧ አማካኝነት ለማድረስ መታቀዱን እና ይህ ቧንቧ ቱርክን ከየብስ ወደ ባሕሩ ዳርቻ እንድትገናኝ በማድረግ ከብሔራዊው የጋዝ መስመር ጋር ለማገናኘት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ቱርክ ኃይልን እንደ ትብብር ቁልፍ እንጂ የውጥረትና የግጭት መስክ እንዲሆን አትፈልግም ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን፡፡
“ቱርክ የኃይል አቅርቦት ዋስትና ችግርን ሙሉ በሙሉ የፈታች ሀገር እስከምትሆን ድረስ በተለያየ መልኩ ትግላችንን እንቀጥላለን ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ቃል መግባታቸውን ቲ አር ቲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.