Fana: At a Speed of Life!

ቱርክ ከ2016 መፈንቅለ መንግስት ጋር ተያይዞ 176 ወታደሮች እንዲታሰሩ ትዕዛዝ አስተላለፈች

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2012(ኤፍቢሲ) ቱርክ ከ2016 መፈንቅለ መንግስት ጋር ተያይዞ 176 ወታደሮች እንዲታሰሩ ትዕዛዝ አስተላለፈች፡፡

እንዲታሰሩ ትዕዛዥ የተላለፈባቸው ወታደሮች መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው እና መፈንቅለ መንግስቱን እንዳቀነባበረ የሚነገረው የፈቱላህ ጉለን አባላት እንደሆኑ ተነግሯል፡፡

በቱርክ  የፈቱላህ ጉለን አባላት ላይ የሚካሄደው ዘመቻ አሁን ተጠናክሮም እንደቀጠለ ነው የሚነገረው፡፡

በዛሬው ዕለት በሀገሪቱ ምእራባዊ ከተማ ኢዝሚር የጀመረው ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ዘመቻ በ49 ሌሎች ከተማዎች እየተካሄደ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በቁጥጥር ስር እየዋሉ ከሚገኙት ወታደሮች 143 ሌተናቶች ፣ 33 ዝቅተኛ ሌተናቶች እና ሲክስ ኤፍ 16 የጦር አውሮፓላን አብራሪዎች መሆናቸው ተነግሯል፡፡፡

ከዚህ መፈንቅለ መንግስት ጋር ተያይዞ በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የፍርድ ሂደት በመጠባበቅ ላይ ሲሆኑ 150 ሺህ የሚሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ፣ ወታደራሮች እና ሌሎችም ከሥራ ተባረዋል ፡፡

ከፈረንጆቹ 1999 ጀምሮ በስደት በፔንሲልቫኒያ  የሚኖሩት የሃይማኖት መሪው ፈቱላህ ጉለን በተደረገው መፈንቅለ መንግስት ሙከራው ምንም ዓይነት ተሳትፎ እንዳልነበራቸው ይገልፃሉ፡፡

መንግሥት ድርጊቱ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ተቃውሞ ለማስቆም ተጠቅሞበታል የሚሉ አሉ ፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.