Fana: At a Speed of Life!

ቱርክ ወታደሮቿን ወደ ሊቢያ መላክ ጀመረች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቱርክ ፕሬዚዳናት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን የሀገሪቱ ወታደሮች ፓርላማው ያሳላፈውን ውሳኔ ተከትሎ ወደ ሊቢያ ማቅናት መጀመራቸውን አስታወቁ።

ወደ ሊቢያ ማቅናት የጀመሩት ወታደሮች ተልዕኮ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚደገፈውን የትሪፖሊ መንግስት አስተዳደር በመደገፍ ሰላምና መረጋጋትን ማስፈን ነው ብለዋል።

ይህ አለም አቀፍ እውቅና ያለው የትሪፓሊ መንግስት መቀመጫውን በምስራቅ ሊቢያ ካደረገው የጄኔራል ካሊፋ ሃፍታር ጦር ጋር ከፍተኛ ፍልሚያ እያካሄደ ይገኛል።

ጄኔራል ሀፍታር በግብፅ እና በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ሲደገፍ፤ በተመድ የሚደገፈው የትሪፓሊ አስተዳደር ደግሞ በቱርክ እና ኳታር ይደገፋል።

በጄኔራል ሀፍታር የሚመራው የአማፂ ቡድን በአሁን ወቅት ትሪፓሊን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገ ይገኛል።

አማፂ ቡድኑ ባለፈው ቅዳሜ በወታዳራዊ አካዳሚ ተፈጽሞ 30 ሰዎች የተገደሉበትን የአየር ጥቃት ፈፅሟል የሚል ወቀሳ የሚቀርብበት ሲሆን፥ ቡድኑ ግን ወቀሳውን አጣጥሏል።

ቱርክ በሊቢያ ወታደሮቿን ማሰማራው ለጦርነት ሳይሆን ህጋዊውን መንግስት ለመደገፍ እና ሰብዓዊ ቀውስን ለማስቀረት ነው ስትል አስታውቃለች።

ምንጭ፡- ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.