Fana: At a Speed of Life!

ቱርክ የስዊዲንና ፊንላንድ ኔቶን የመቀላቀል ፍላጎት በአዎንታ እንደማትመለከት ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን ስዊዲንና ፊንላንድ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ሀገር ለመሆን ላሳዩት ፍላጎት አዎንታዊ አስተያየት እንደሌላቸው አስታወቁ።
ለዓመታት ከብዙ መሰል ህብረቶች ገለልተኛ ሆነው የኖሩት ሁለቱ ሀገራት የሩሲያ- ዩክሬን ግጭትን ተከትሎ ኔቶን እንቀላቀላለን ብለዋል።
ይህም ፍላጎታቸው በሩሲያ ዘንድ ቁጣን የቀሰቀሰ ሲሆን፥ ለዚህ ውሳኔያቸው ጠንካራ ምላሽ እንደምትሰጥ ሞስኮ አስጠንቅቃለች።
ዛሬም ሞስኮ ለፊንላንድ የምታቀርበውን የኤሌክትሪክ ሀይል አቋርጣለች።
ኔቶ አፍንጫዬ ውስጥ መጥቶ የጦር መሳሪያዎቹን እንዲተክል አልፈቅድም ባይ ናት ሩሲያ።
የኔቶ አባል የሆነችው ቱርክም የሀገራቱን መቀላቀል የወደደች አይመስልም።
ነገ በይፋ ማመልከቻቸውን ለኔቶ ያስገባሉ የተባሉት የስዊዲንና ፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችም ከአንካራ የገጠማቸውን ተቃውሞ ለማለሳለስ ዛሬ በበርሊን ከቱርክ አቻቸው ጋር ይመክራሉ መባሉን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.