Fana: At a Speed of Life!

ቲክቶክ የማይክሮሶፍትን ጨረታ ውድቅ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቲክቶክ የማይክሮሶፍትን ጨረታ በመጨረሻ ሰዓት ውድቅ ማድረጉ ተነገረ።

አጭር ቪዲዮን የማጋራት አገልግሎት የሚሰጠው ቲክቶክ የማይክሮሶፍትን ጨረታ በመጨረሻ ሰዓት ውድቅ ማድረጉ ተሰምቷል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቻይና ባለቤትነት የተያዘው መተግበሪያ እንዲዘጋ ለመስከረም 15 ቀን ቀጠሮ መስጠታቸው ይታወሳል።

የትራምፕ አስተዳደር ቲክቶክ እና ሌሎች የቻይና መተግበሪያዎች የሀገር ደህንነት ስጋት ናቸው ይላል።

በዚህም ፕሬዚዳንት ትራምፕ ቲክቶክ መተግበሪያ ከአሜሪካ ይታገዳል ማለታቸውን ተከትሎ ማይክሮሶፍት የቲክቶክ የአሜሪካ ድርሻን ለመግዛት ድርድር እያደረገ መሆኑ የሚታወስ ነው።

ማይክሮሶፍት እና ኦራክልም ቲክቶክን ከቻይናው ኩባንያ ባይቴዳንስ ለመግዛት ጨረታውን መርተው ነበር።

ነገር ግን አሁን ቲክቶክ በመጨረሻው ሰዓት  የማይክሮሶፍትን ጨረታ  ውድቅ አድርጊያለው፤ቲክቶክን ለማይክሮሶፍት አልሸጥም ሲል አስታውቋል፡፡

ይህን አስመልክቶም አንድ የቲክቶክ ቃል አቀባይ፥ ስለ ማይክሮሶፍት ልማትም ሆነ ስለ ኦራክል ግምታዊ አስተያየት አልሰጥም ብለዋል።

ማይክሮ ሳፍት በበኩሉ “እኛ ያቀረብነው ሀሳብ የብሔራዊ ደህንነት ጥቅሞችን በማስጠበቅ በኩል ለቲኪቶክ ተጠቃሚዎች ጥሩ እንደሚሆን እርግጠኞች ነን” ብሏል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.