Fana: At a Speed of Life!

ታላቁ የግብፅ ኢማም የህዳሴ ግድብን አስመልክተው የሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያን ሀቅ የካደ ነው – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ታላቁ የግብፅ ኢማም የታላቁ ህዳሴ ግድብን በሚመለከት የሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያን ሀቅ ያልተመለከተና እውነት የጐደለው ነው ሲሉ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ ገለጹ።

ከሰሞኑ የግብፁ ዓለም አቀፋዊ እስልምና ተቋም ታላቅ ኢማም የሆኑት ሼክ አልአዝሀር- አህመድ ጠይብ የህዳሴ ግድብን በሚመለከት ኢትዮጵያ ወንዙን በብቸኝነት በመጠቀም ሌሎች ሀገራት ላይ ጉዳት ለማድረስ እየሰራች መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል፡፡

የኢማሙ ንግግር ከእውነት የራቀና ተቀባይነት የሌለው መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ ተናግረዋል።

መግለጫውም የኢትዮጵያን ሀቅ ያልተመለከተና የመንግስትን አቋም የማይገልፅ ነው ሲሉ ውድቅ አድርገውታል።

ኢትዮጵያ ሁልጊዜም ውሃውን በፍትሃዊነት እንጠቀም የሚል አቋሟን ስትገልፅ ከርማለች ያሉት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ÷ ግብፅና ሱዳንም ይህንን እውነት ይዘው ወደ ሰላማዊ ድርድር እንዲመጡም ጥሪ አቅርበዋል።

የአባይ ውሃ ምንጩም ተፋሰሱም በአፍሪካ ምድር በመሆኑ መፍትሄውም እዚሁ ነው ሲሉ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.